ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመልካም ጉርብትና እንኖራለን – የቆራሪት ከተማ ነዋሪዎች 

ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመልካም ጉርብትና እንኖራለን – የቆራሪት ከተማ ነዋሪዎች 

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳደር  ከቆራሪት ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ከአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት  ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መጋቢት 19ቀን2024 መክረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የቆራሪ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች የከተማዋ ኅብረተሰብ የአካባቢያቸውን አንጻራዊ ሰላም  በንቃት እያስጠበቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል። 

“ጠላታችን ሕወሓት እንጅ የትግራይ ሕዝብ ባለመኾኑ ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመልካም ጉርብትና እንኖራለን ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች የአማራ ሕዝብ ዋጋ የከፈለበት የማንነት እና የወሰን ጥያቄ መንግሥት በሕግ የእውቅና ምላሽ ሊሰጥ ይገባል። “ብለዋል።

ነዋሪዎቹ በውይይት መድረኩ ላይ በከተማዋ በ2013 ዓ.ም በሰሜኑ ጦርነት በደረሰው ጉዳት የመልሶ ማቋቋም ሥራ ባለመከናወኑ የመብራት፣ የባንክ፣ የአንቡላንስ እና የኔትዎርክ አገልግሎት ከሦስት ዓመት በላይ በመቋረጡ እየተቸገሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ችግራቸውን መንግሥት እንዲቀርፍላቸውም ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ከፋኝ ብሎ ለበርካታ ዓመታት በመታገሉ ዛሬ ላይ ነጻነቱን አግኝቷል ብለዋል። በቀጣይም አንድነታችሁን በማጠናከር ነጻነታችሁን አጽንታችሁ ልትጠብቁ ይገባል ነው ያሉት።

የአማራ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን እንዲሁም የዞኑ የበጀት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መኾኑንም በውይይቱ ላይ የተገኙ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ለነዋሪዎች መናገራቸው ታውቆል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY