ክርስቲያን ታደለ እና ሌሎች እስረኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ 

ክርስቲያን ታደለ እና ሌሎች እስረኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ክርስቲያን ታደለ ፣ ዮሐንስ ቧያለው እና ካሳ ተሻገር እና ሌሎች አስራ አንድ ተጠርጣሪዎች በድምሩ አስራ አራት ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ቀረቡ።

ዛሬ ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የፖለቲካ ርዕዮታቸውን በኃይል ለማስፈጸም በማሰብ፣ በኅቡዕ የተቋቋመውን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማዎች ለማስፈጸምና ‘የአማራ ሕዝብ ርሥቶች ናቸው’ የሚሏቸውን አካባቢዎች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስ የተደራጁ ነበሩ” ሲል  ዓቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ።

በዚህ ክስ መዝገብ ስርም  ጫኔ ከበደ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዘመነ ካሴ፣ አበበ ፈንታው፣ አሰግድ መኮንን፣ መከታው ማሞ፣ ፈንታሁን ሙሃባ እና ሌሎችም የተካተቱ ሲሆን፣ ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል ለስምንት ወራት በእሥር ላይ የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ናቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በዚሁ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች 14 ተጠርጣሪዎችም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግስት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርበው የክስ መዝገባቸውን መቀበላቸው  38ተጠርጣሪዎች በሌሉበት ነው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ታውቋል።(EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY