በራያ በ10 ሺህዎች የሚጠጉ ነዋሪዎች ዳግም መፈናቀላቸዉ ተነገረ 

በራያ በ10 ሺህዎች የሚጠጉ ነዋሪዎች ዳግም መፈናቀላቸዉ ተነገረ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሰሞኑን በራያ አላማጣ ወረዳ አንዳንድ አካባቢዎች ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በ10ሺህ የሚቆጠሩ የአላማጣና ኮረም ነዋሪዎች ወደ ቆቦና ሰቆጣ መፈናቀላቸውን ተናገሩ።

ከአላማጣ ከተማ  ወደ ቆቦ እንደተፈናቀሉ በሰሞኑ ግጭት ሰለባ  እንዳይሆኑ ቀያቸውን የለቀቁ ተፈናቃዬች እንዴት ናችሁ ያለን አካል የለም፣ በየበረንዳውና በየመንገዱ ተበትነናል ብለዋል። በመንገድ ላይ ከየት እንደተተኮሰ በማይታወቅ ጥይት ተመትተው የሞቱ ሠዎች እንዳሉም አመልክተዋል። 

እንደ አስተያየት ሰጪው 10ሺህ ያክል ሰዎች ከአላማጣ ቆቦ ገብተዋል። እንደዚሁም ከኮረም ከተማ የሚፈናቀሉ ሠዎች ሰቆጣ ከተማ መግባታቸውን ትናንት ስቆጣ የደረሱ ተፈናቃዮች ተናግረዋል።

የፀጥታ አካላት አባላት ተፈናቃዮችን አትሂዱ እያሉ ሲመልሷቸው መመልከታቸውንም ተነግረዋል።

የወሎ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ሊቀመንበር ሰሞኑን የ  የትግራይ ተዋጊዎች የራያ፣ አላማጣ፣  ኮረም ከተሞችን መቆጣጠር ባይችሉም በየተራሮቹ ላይ ስፍረው ለዳግም ውጊያ እየተዘጋጁ ነው። ህብረተሰቡም  ዳግም ጦርነት ስለባ እንዳይሆን  በመፍራት  ከቀዬውእየተፈናቀለ እንደሆነ ተናግረዋል።(EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY