በጁባ ኢትዮጵያዊው የታሽገ ውሃ ፋብሪካ ኃላፊ ተገደለ

በጁባ ኢትዮጵያዊው የታሽገ ውሃ ፋብሪካ ኃላፊ ተገደለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ኦሲስ የታሽገ ውሃ ፋብሪካ  ማናጀር ኢንጂነር ወልደፂዮን ግደይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ አስከሬኑ ተጥሎ መገኝቱን  አይ ሬዲዬ ዘገበ።

ኢንጂነር ወልደፂዮን  ግዳይ በ 1980 ዓ.ም በኩባ ሳንቲያጎ ዩኒቨርስቲ የኢንጂነሪንግ ፋኩልቲ ከተመረቀ በኋላ በመጀመሪያ በአሥመራ ሳባ መሥታወት ፋብሪካ በኋላ በአዲስ አበባ ጠርሙስና ብርጭቆ ፋብሪካ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ያገለገለ ሲሆን በኢትዮ-ኤርትራ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ወደ ኤርትራ በማቅናት ከዛም ወደ ደቡብ ሱዳን በማምራት  የ ታሽገ ውሀ ፋብሪካ በመክፈት  የተሳካ የንግድ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደነበር ወዳጆቹ ይናገራሉ።

የጁባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንጂነር ወልደፅዬን ግዳይ አስከሬን  ምርመራ ማድረጉንና የገዳዩን ማንነት በማጣራት ላይ መሆኑን  የአይ ሬዲዮ ዘግቧል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY