በትግራይ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቅረፍ የእርዳታ ጥሪ ቀረበ 

በትግራይ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቅረፍ የእርዳታ ጥሪ ቀረበ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ እየደረሰ ባለው አስከፊ ቀውስ ለመቅረፍ አስቸኳይ የሰበአዊ እርዳታ እንዲደረግ በአዲግራት የኢትዩጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ኤጲስቆጶስ  አባተስፋሥላሴ መድህን  ተማጽኑ።

ኤጲስ ቆጶስ ተስፋሥላሴ መድህን በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለዓመታት በዘለቀው ግጭት፣ ድርቅና ዳተኝነት  ሕዝቡ በተለይም በሴቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ፣ ተስፋ መቁረጥ እና መፈናቀልና ስደትን  አስከፊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጉልተው አሳይተዋል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በጦርነቱ የተፈናቀሉ እና በአሁኑ ወቅት ትግራይ እና አጎራባች ክልሎች መጠለያ ውስጥ በስጋት ለአስከፊ ስነልቦና ቀውስ ተዳርገው በመኖር ላይ  ናቸው  ሲሉ ስለአለው መኅበራዊ ቀውስን በዝርዝር ገልፀዋል። 

ኤጲስ ቆጶስ ተስፋ ስላሴ መድህን  በአሁኑ ወቅት የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እየተደረገ ያለው ጥረት በቂ አለመሆኑን፣ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እየጨመረ በመምጣቱ እና አንገብጋቢ የሆኑ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት መንግስትና የሚመለከታቸው ተቁዋማት እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ችግሩን ለመቅረፍ ቁርጠኝነት እንደሚያንሳቸው  በአሰራጩት ግልፅ ደብዳቤ ላይ አስምረውበታል።  .

ኤጲስ ቆጶስ ተስፋስላሴ መድህን በኤፕሪል 15 ቀን2024 በተጻፈው በቫቲካን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት በተስራጨው ደብዳቤ ላይ ያቀረቡት የተግባር ጥሪ ለትግራይ እና አጎራባች ክልሎች ለከፋ ሰበአዊና መኅበራዊ ቀውስ ተጋላጭ የሆኑ ህዝቦችን ለመደገፍ ተጨማሪ ግብአት  ያስፈልጋል። ይህንን ፍላጎት ለማሞላት አለም አቀፉ መኅበረሰብ ሊረባረብ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ተማፅነዋል።

የአዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኤጲስ ቆጶስ ስ በአፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ  ለሚሹ ወገኖች ፣በማዳረስ  የክልሉን ሰፊ ተግዳሮቶች ለመፍታት ብቸኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።የችግሩን ውስብስብ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና መንፈሳዊ ገፅታዎች በመገንዘብ ትግራይን እና አጎራባች ማህበረሰቦችን በአማራ እና አፋር ህዝቦች ላይም  የደረሰውን ችግር እልባት ለመስጠት መረባረብ ይኖርበታል ሲሉ ጥሪ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ከኤርትራ ጋር በሚዋሰኑ የድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ  እንደ ኢሮብ እና ኩናማ ያሉ ማህበረሰቦች አሁን ድረስ በጦርነት ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። እንድረስላቸው ሲሉ አለም አቀፉን መኅበረስብ  ተማፅነዋል።(enእትዩጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY