የተባበሩት መንግስታት የአላማጣና የራያ ተፈናቃዮች ህልውና ለአደጋ ተጋልጧል አለ

የተባበሩት መንግስታት የአላማጣና የራያ ተፈናቃዮች ህልውና ለአደጋ ተጋልጧል አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (ኦቻ)በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ   (ኦቻ) አስታወቀ። 

አብዘሃኛው ህጻናት እና ሴቶች የሆኑ 23ሺ ተፈናቃዮች ቆቦ፣ 5ሺ 980 የሚሆኑት ደግሞ ሰቆጣ ከተማ ተጠልለዋል ያለው ቢሮው በአከባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም የተረጋጋ ባለመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርት ጠቁሟል። 

የምግብ እና ውሃ እጥረቱ አሳሳቢ ነው ያለው ቢሮው አፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል። 

ሜዳ ላይ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃይ ቤተሰቦች በመኖራቸው ከለላ ሊሰጣቸው ይገባል ብሏል። 

ቢሮው እና አጋር ተቋማት ያላቸው አቅርቦት ውስን በመሆኑ የአከባቢው ማህበረሰብ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እጅግ ለተጎዱት የምግብ እና ውሃ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል። 

ዘርፈ ብዙ እገዛ በአፋጣኝ ሊደረግላቸው እንደሚገባ የጠየቀው ቢሮው በተለይም መጠለያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እንዲሆን ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችላቸው እገዛ እንዲደረግላቸው አሳስቧል።(EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY