ኬኒያ ቆሻሻን በፌስታል መጣልን በህግ አገደች 

ኬኒያ ቆሻሻን በፌስታል መጣልን በህግ አገደች 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኬንያ ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን (ነማ) ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ፌስታሎች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።

በኤፕሪል 8/2024  የኬንያ ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን  በወጣው ማስታወቂያ ላይ ኬንያውያን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፕላስቲክ ከረጢቶችን ፌስታሎች መጠቀም ለማቆም 90 ቀናት አላቸው።

“ስለዚህ ከላይ ለተጠቀሰው እና የአካባቢን ጤናማ የኦርጋኒክ ቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ለማረጋገጥ የኬኒያ  ባለሥልጣኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ መመሪያ ይሰጣል፡-

ኬንያ በ2017ከዛሬ ሰባት አመት በፊት የፕላስቲክ እቃ መያዥያ ፌስታሎችን መጠቀም መመረት ከልክላ የነበረ ቢሆንም አፈፃፀሙ ላይ ችግሮች መከሰታቸውን ዘገባዎች ያስረዳሉ።  

አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች እና ዋና ተጠቃሚዎች እገዳውን አክብረውታል፣ ነገር ግን ፌስታሎቹ ሙሉ በሙሉ ከገበያ አልተወገዱም።  ያሉ አስተያየት  ሰጭ  ባለስልጣኑ ያወጣው ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ፌስታሎች መጠቀም ከዘጠና ቀናት በኃላ  የተከለከለ መሆኑን ተፈፃሚ ይሆናል አይሆንም  በጊዜው የሚታይ ይሆናል ብለዋል ። (enኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY