Sunday, April 26, 2026

Amharic Posts

Amharic Posts

“በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ችግሩ እንቀጠለ ነው” አፍሪካ ኮንፊዴንሽያል

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በኢትዮጵያ የገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ፓርላማ ለአስር ወራት ጥሎት የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካነሳው አንድ ወር ቢሆነውም በሀገሪቱ ውስጥ...

ግሸን መድሀት ቤትና የዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ውዝግብ መቋጫ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ቀደም ሲል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነሐሴ 4 2017 ባወጣው የምርመራ ዘገባ ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይንም ዶፒንግ ጋር በተያያዘ...

ታሪክን የኋሊት-ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ዝነኛው የ“ሕልም አለኝ” ንግግራቸው /የኔነህ ከበደ/

በቀደመው ዘመን አፍሪካ አሜሪካውያን ከባርነት ቢላቀቁም በዘር ላይ ከተመሰረተው ዓይነተ ብዙ መድልዎና ጭቆና ነፃ ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ትግልን ጠይቋቸዋል፡፡ ከነዚህ አይነታቸው የበዛ የመብት ማስከበሪያ ጥረቶቻቸው...

የኦሮሞ ማህበረሰብና ቄሮዎች መንቃት አለባቸው /ግርማ ካስ/

አንደኛ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥያቄዎችን ከሌሎች ማሀብረሰብ ጥያቄዎች ጋር በማቀናጀት ትግሉን አገር አቀፍ ማድረጉ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት አለበት። በኦሮሚያ ለ5 ቀናት ታዉጆ የነበረው አድማ በ 3...

የሳዉዲ አረቢያ መንግስት 450 ሽህ ኢትዮጵያንን በሀይል ለማስወጣት ማቀዱን አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን 450 ሽህ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በሀይል ከሀገሩ ለማስወጣት እቅድ ማውጣቱን አስታወቀ። እስካሁን 160 ሽህ ኢትዮጵያዊያን...

ሙስናን ወቅት ጠብቆ በሚደረግ ዘመቻ ማስወገድ ይቻላል? /ሀ. ህሩይ – ከቶሮንቶ/

ነሐሴ, 2017 መንግሥት ሙስናን ለመከላከል እና ለማጥፋት የፌዴራል የሥነምግባር እና ፀረ ሙስና ዓዋጅን ካወጣ እና ኮሚሽኑን ካቋቋም በርካታ ዓመታት ሆኗል። ይሁን እንጂ ይህ ዓዋጅ በየግዜው ማሻሻያ...

በ1929 ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ዳግም በወረረችበት ወቅት /ቭሮኒካ መላኩ/

ጊዜው 1929 ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ዳግም በወረረችበት ወቅት ነው ። ራስ ካሳ ሀይሉ ጎንደር ደብረታቦር ካለው ማዘዣ ጣቢያቸው የክተት አዋጅ አስነግረው ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ወራሪው...

መንግሥት የማቋቋም ችግር /ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ/

አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፤ የኢትዮጵያ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ሥራ ስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፤ በሸንጎው የፖለቲካና የጥናት ኮሚቴ “በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር ተኮር የክልሎች አሸናሸንና ዕንድምታው” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ጥናታዊ ሰነድ ላይ አቶ ካሣሁን ነገዎ በአውስትራሊያው የአማርኛ ራዲዮኑ ላቀረበለት ጥያቄዎች የሰጣቸውን መልሶች ያልሰማ እንዳለ እንዲሰማቸው ሐሳብ ላቅርብ። ከውይይቱ እንደተረዳሁት፥ ጥናቱ የሚደገፍና የሚመሰገን ነው። ግን መደምደሚያውን ከሀገሪቱ ታሪክ ጋር አያይዞ በመደምደም ፈንታ ለሌላ ለአወዛጋቢ ጊዜ አስተላልፎታል። ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ። አንደኛው የተማሪዎቹ ንቅናቄ ባመጣብን “ብሔር፥ ብሔረ ሰብ” በሚለው አነጋገር ላይ የሚያተኩር ነው። ካሁን በፊት እንደተቸሁት፥ እነዚህ ቃላት የተፈጠሩት የኛን “ጎሳ፥ ነገድ” በመናቅ ስለ ሆነ ከፖለቲካ መዝገባ ቃላታችን አውጥተን መጣል አለብን። የራስን መናቅ ራስን መናቅ ነው። ራስን የሚንቅ ሕዝብ ሌሎችን አምላኪ ሆኖ ይቀራል። ሁለተኛውም የምዕራባውያን ባህል ተጽዕኖ ባመጣብኝ ችግር ላይ የሚያተኩት ነው። ይኸውም “አገራችን ላይ የሚዘረጋው አስተዳደር አሐዳዊ ይሁን ወይስ ፌዴራዊ” የሚለው ጥያቄ ነው። አሐዳዊ ከሆነ ጎሳዎችና ነገዶች እንዴት ይስተናገዱ? ፌዴራዊ ከሆነ አገሪቱ እንዴት ትከፋፈል? እያልን እንተቻለን። ይኼ ትችት እኮ፥ ብናውቀውም ባናውቀውም፥ በታሪካችን ላይ የሚደረግ ዘመቻ ነው። ታሪካችን አገሪቱን ከፋፍሎ ለያንዳንዳቸው ክፍለ ሀገር ስም (አስተዳደርም) ሰጥቶታል። የሚከበር፥ የሚጠበቅ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ አስተዋጽዖ ነው። ክፍለ ሀገሮቹን እንዳሉ ጠብቆ አሐዳዊ ወይም ፌዴራዊ የዲሞክራሲ አስተዳደር ለመዘርጋት የማይቻልበት ምክንያት የለም። ዋናው ነገር፥ ክፍለ ሀገሮቹ ራስ-ገዝና ለማእከላዊው መንግሥት ታዛዥ እንዲሆኑ መስማማት ነው። ሁለተኛው ዋና ነገር፥ ማንም ኢትዮጵያዊ ከማንኛውም ክፍለ ሀገር ለመኖር ምን ጊዜም መብቱ መሆኑን ማመን ነው። ይኸ “የነገድ (የዘረኝነት) መንግሥት መሥርተን የጎሳዎችን መብት እንጠብቃለን” የሚሉት አነጋገር፥ የጎሳዎችን መብት መጣስ ነው። ማንም ኢትዮጵያዊ ለማንም ኢትዮጵያዊ መብት የመስጠትና የመንፈግ መብት የለውም። ማን ከማን አንሶ! ማን ከማን በልጦ! የክፍለ ሀገሩን አስተዳደር የሚቀይሱ በክፍለ ሀገሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ እንጂ የነገዶቹ የግል መብት አይደለም። የሚቀይሱትም እንደ ጎሳነታቸው ወይም እንደ ነገድነታቸው ሳይሆን፥ እንደ ገለሰብ የአካባቢው ዜግነታቸው ነው። የጎሳ ወይም የነገድ (ወይም የሃይማኖት) ማንነታቸው የግል ስለ ሆነ፥ ጎሳንና ነገድን (ሃይማኖትን) የሚገድ ጥያቄ ሲነሣ ጎሳዎችና ነገዶች ጉዳያቸውን ከመንግሥት አስተዳደር ውጪ ይነጋገሩበት።

አዲስ አበባ በረራ ናት፤ በረራም አዲስ አበባ /አምባ የጥናት እና ምርምር ክፍል/

ረቂቅ:- በሀቅ ላይ የተመሰረተ ታሪክ ጽኑ የአንድነት መሰረት ነው። ፍትህንም ለማስፈን ወሳኝ ሚና አለው። ታሪክ የራሱ የሆነ የሙያ ስነምግባር አለው። የታሪክ ባለሙያ ለሙያው ፍቅርም ሲል...

በጅማ ከተማ በቦምብ ጥቃት 13 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በጅማ ከተማ እኩለ ቀን አካባቢ በተጣለ የእጅ ቦንብ በ13 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል። ቦንቡ የተጣለው ለገሃር ተብሎ...

Poems